በደቡብ አፍሪካ የገዥው ፓርቲ ኤኤንሲ ብሄራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጃኮብ ዙማን በአባልነት ለማገድ መወሰኑን አስታውቋል።
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ዙማ በፓርቲው የዲሲፕሊን ኮሚቴ ነው ውሳኔ የተላለፈባቸው፡፡
ባለፈው ታህሳስ ዙማ አዲስ የተቋቋመውን MK ፓርቲ እንደሚመርጡ በይፋ አስታውቀው ነበር።
አዲሱን ፓርቲ በማፅደቅ ረገድ ዙማ የፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳን እና ኤኤንሲ ፓርቲን መደገፍ እንደማይፈልጉ መናገራቸውና መተቸታቸው ለዲስፕሊን ኮሚቴው እንዲቀርቡ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡
በዚህ ዓመት በሚደረገው ምርጫ ዙማ አዲሱን ፓርቲ ወክለው እንደሚወዳደሩ እየተናገሩ ነው፡፡
እንደ አፍሪካ ኒውስ ዘገባ ፤ በ2024 የሚደረገው የደቡብ አፈሪካ አጠቃላይ ምርጫ ከፍተኛ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv