አዲስ አበባ | ጥር 20፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የዓለማችን ትልቁ የሽርሽር መርከብ ጉዞውን ለመጀመር ከማያሚ ፍሎሪዳ ግዛት ተነስቷል ፤ ነገር ግን መርከቡ የሚቴን ልቀት ስጋት እንዳለበት ተነግሯል።

7,600 መንገደኞችን መያዝ የሚችለው መርከብ በሮያል ካሪቢያን ግሩፕ ባለቤትነት የተያዘ እንደሆነ ታውቋል።
መርከቡ በካሪቢያን ለሰባት ቀናት የሚፈጀውን የደሴት ጉዞ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
በፊንላንድ እና ቱርክ የመርከብ ጣቢያ የተገነባው የሽርሽር መርከብ ሰባት የመዋኛ ገንዳዎች እና ስድስት የውሃ ማፋሰሻ አሉት።
ግንባታውን ለማጠናቀቅ 2 ቢሊዮን ዶላር የፈጀ ሲሆን ከ40 በላይ ሬስቶራንቶች እና ላውንጆች እንዳሉትም ተነገሯል። ዘገባው የቢቢሲ ነው
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












