አዲስ አበባ | ጥር 20፤ 2016| NBC ETHIOPIA-በሱዳን በሁለቱ ሀይሎች መካከል እየተደረገ በሚገኘው ጦርነት፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ፤ ሞሃጀር 6 የተባለ ኢራን ሰራሽ ሰው አልባ አውሮፕላን መትቶ መጣሉን አስታውቋል ፡፡
የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ በኤክስ በቀድሞው ትዊተር እንዳሰፈረው በካርቱም፤ ኦምብዱርማንና ባህሪ በሚባሉ ቦታዎች ላይ ውጊያ እያደረገ ነው፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ፤ በሁለቱ ቡድኖች በሚደረገው ውጊያ፤ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ድል እየቀናኝ ነው ቢልም፤ ከሱዳን ጦር ሰራዊት በኩል ግን ምንም የተባለ ነገር እስካሁን የለም፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












