አዲስ አበባ | ጥር 09፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ኢትዮ ቴሌኮም የዜድቲኢ ብሌድ ቨርዥን V50 ዲዛይንን ጨምሮ A40 እና A54 ስማርት ስልኮችን ለደንበኞች ማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ከዜድቲኢ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።

ኩባንያው የደንበኞችን ፍላጎት እና ተሞክሮ ለማሳደግ እንዲሁም የዲጂታል አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ለማስቻል የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ከዜድቲኢ ኩባንያ ጋር በትብብር ስማርት ስልኮችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ ስለመቻሉ ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ስማርት ስልኮችን ተደራሽ ለማድረግ እና አጠቃላይ የዜጎችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስማርት ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ በተለያዩ የመክፈያ ዘዴዎች ማቅረቡን የኢትዮ ቴሌኮም የቴክኖሎጂ ዘርፍ ዋና ሀላፊ ታሪኩ ደምሴ ተናግረዋል።
በሀይማኖት ወርቁ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












