
በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ የኢንስቲትዩት ኦፍ ሂማን ኦርጂን ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ዩሀንስ ሀይስላሴ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ቅሬተ አካሉ የተገኘበት 50ኛ አመት በተለያዩ የሲንፖዚየም፣ ኤግዚቢሽን መርሀግብሮች እንደሚከበር አስታውቀዋል።
የፈረንጆቹን አዲስ አመት መግባቱን ተከትሎ ከተያዘው የጥር ወር ጀምሮ እስከ ሚቀጥለው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ድረስ በኢኒስቲትዩቱ አነሳሽነት አመቱን ሙሉ እንደሚከበር ፕሮፌሰሩ ገልፀዋል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተነሳሽነቱን በመጋራት በዓሉን በተለያዩ መርሀግብር እንዲያከብሩት ፕሮፌሰር ዩሀንስ ጥሪ አቅርበዋል።

የሉሲን ቅሬተ አካል ባገኘው ፕሮፌሰር ዶናርድ ሮቢንሰን የተጋበዙ እንግዶች የሉሲን ቅሬተ አካል እና የኢትዮጵያ የኃሊት የሚያስመለክቱ ቅርሶችን ጎብኝተዋል።
ሉሲ (ድንቅነሽ) ቅሬተ አካሏ የተገኘው ኅዳር 14 ቀን በ1967 ዓ.ም ሲሆን ቁመቷ 105 ሴ.ሜ እንደሆነ ግኝቱ ያመላክታል።
እድሜዋ 3.2 ሚሊዮን አመት እንደሆነ የምትገመተዉ ሉሲ በአፋር ክልል አዋሽ ሸለቆ ሃዳር አከባቢ ነው የተገኘችው።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












