Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

የድባቴ ህመም ምንድን ነው?

January 16, 2024
in Health
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ጥር 07፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ድባቴ በማንኛውም ዕድሜ ፣ ዘር ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የትምህርት ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡

ለመሆኑ ድባቴ  ምንድን ነው?

የድባቴ  ከተለመደው የስሜት ለውጥ እና የእለት ከእለት የህይወት ፈተናወች ምክንያት ከምናሳየው የስሜት መልስ ይለያል። ድባቴ በአንድ ሰው አስተሳሰብ ፣ ስሜት እና በተግባር ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሀዘን ፣ ገለልተኛነት እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ተለይቶ የሚታወቅ የአእምሮ ሁኔታ ነዉ።

ድባቴ ደስታን በሚያመጡ ነገሮች ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ማጣትን ያመጣል። የአንድን ሰው ሀሳቦች ፣ ባህሪ ፣ ተነሳሽነት ፣ ስሜቶች እና ደህንነትንም ይለውጣል፡፡ ድባቴ ያጋጠማቸው ሰዎች የመጥፎ ስሜት ፣ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይኖራቸዋል እናም በአንድ ሰው የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፣ ከፍ ሲልም ራስን የማጥፋት ሀሳቦችን ሊኖሯቸው ይችላል።

የድባቴ  ህመም ዓይነቶች

1.ከባድ የድብርት ህመም ድባቴ (major depression disorder) –

ከባድ የሀዘን ወይም የፍላጎት ማጣት፣ የጭንቀት ስሜት ፣ ድካም ፣ በእንቅልፍ ላይ ለውጦች ፣ ክብደት መቀነስ ፣ትኩረት ማጣት፣ የከንቱነት እና የጥፋተኝነት ስሜቶች ፣ በተለመዱ እንቅስቃሴዎች ላይ ፍላጎት ማጣት ፣የሞት እና ራስን የማጥፋት ሀሳቦች ለሁለት ሳምንት በየቀኑ በሚባል ደረጃ ይታያሉ (ክብደት መቀነስ እና ራስን ከማጥፋት ሀሳብ ውጭ) ።

2. የማያቋርጥ ድባቴ (dysthymia) :-

ቢያንስ ለሁለት ዓመታት (1 አመት ለህጻናት) የሚታይ ሥር የሰደደ የድብርት ዓይነት ነው። በነዚህ ሁለት አመታት ህመሙ ያለባቸው ሰወች ያለ ድብርት ምልክቶች ከሁለት ወራት በላይ አይቆዩም።

3, የሚረብሽ የስሜት መለዋወጥ (disruptive mood dysregulation) ህመሙ ያለባቸው ሰዎች ቁጣ ፣ መገንፈል ፣ንዴት እና መበሳጨት የሚያመጣ የድባቴ አይነት ነው።

4.ቅድመ የወር አበባ ዲስፎሪክ ህመም (Premenustral dysphoric disorder) :-

የድባቴ ምልክቶቹ ከወር አበባ በፊት ባለው ሳምንት በግልጽ በሚታይ ወይም በምርመራ ሊታወቅ በሚችል መልኩ ይታያል ይህም ስራ የመስራት አቅምን ይቀንሳል ፤ማህበራዊ ወይም ቤተሰባዊ ትስስርን ይጎዳል።

5.በመድሀኒቶች ምክንያት የሚመጣ ድባቴ (substance /medication induced depressive disorder) –

አደንዛዥ እፅ ፣ መርዝ፣የአዕምሮ በሽታ መድኃኒቶችን በመብላት፣በመርፌ ወደ ደም ዝውውር በማስገባት ፣ወይም በመሳብ ጊዜ የሚከሰት ድባቴ ነው።

6. በሌሎች ህመሞች ምክንያት የሚመጣ ድብርት (depression due to other medical conditions) –ለምሳሌ፦ Parkinson ፣ Huntington ፣ stroke ፣ traumatic brain injury ለድባቴ ተጋላጭነትን ይጨምራሉ።

የድባቴ  ህመም መንስኤዎች

-ሐዘን- የሚወዱትን ሰው በ ሞት ማጣት

-ህመም (እንደ የታይሮይድ በሽታ ፣ የአዲሰን በሽታ ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የትኩረት እጦት / hyperactivity Disorder (ADHD)፣ ካንሰር ፣ የጉበት በሽታ )

-የገንዘብ ጫና- የገንዘብ ማጣት የሚፈጥረው ጭንቀት

-አስጨናቂ የሕይወት ክስተቶች – ( አካላዊ ፣ ወሲባዊ ወይም ስሜታዊ በደሎች )

-የተወሰኑ የህክምና መድኃኒቶች – (ለካንሰር፣ለልብ፣Parkinson፣ seizure ህመሞች የሚወሰዱ መድሀኒቶች)

-ስነ-ባህሪ ( genetics ) – እናት ወይም አባት ድብርት ካለባቸው ልጃቸው የመያዝ እድሉ ይጨምራል

-አካባቢያዊ – አስጨናቂ የልጅነት ገጠመኞች

-ባህላዊ እምነቶች  – ወንዶች ማልቀስ የለባቸውም  አይነት ማህበራዊ ጫናዎች

-ጉርምስና – የጉርምስና ዕድሜ በስሜትና በባህሪ ከፍተኛ ለውጦች የሚታይበት እድሜ ነው።

-ገጽ ብቸኝነት – አንድ ሰው ከቤተሰብ ወይም ከጓደኞች ጋር  የማይገናኝ ከሆነ ወይም ከቤተሰቡ ጋር ጊዜ የማያሳልፍ ከሆነ ወይም ቤተሰብ ከሌላቸው

-ልጅ መውለድ – በእርግዝና ወይም ከወሊድ በሗላ በሚለዋወጡ ተፈጥሯዊ ኬሚካሎች ምክንያት እንዲሁም ልጅ ከወለዱ በሗላ በሚመጣው የሀላፊነት ስሜት ምክንያት ድብርት ሊያጋጥም ይችላል።

-የአካል ጉዳተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ለድብርት የመጋለጥ   እድላቸው ከፍ ያለ ነው

የድባቴ  ህመም መንስኤዎች

የድብርት ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው ሊለያዩ ይችላሉ ፣ ግን በብዙ ሰዎች ሊታዩ የሚችሉ የተለመዱ ምልክቶች አሉ፡፡

1.ሀዘን፣ጭንቀት ፣ ወይም ‘ባዶነት’ ስሜት

2. ተስፋ መቁረጥ/ጨለምተኝነት

3. ያልተገባ የጥፋተኝነት ስሜት ፣ጥቅም አልባነት ፣ረዳት አልባነት ስሜት

4 በፊት የሚወዱት እና የሚያስደስት ነገር ላይ ፍቅር መቀነስ ወይም መጥላት

5 ድካምና የሃይል ማነስ

6 የትኩረት ማነስ ወይም አለማስተዋል

7 የእንቅልፍ እጦት ወይም ከልክ በላይ ማንቀላፋት

8.የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና የክብደት ለውጥ

10. ስለ ሞት ወይም እራስን ስለ ማጥፋት ማሰብ ወይም ራስን ለማጥፋት መሞከር

11. ራስምታት ፣ ህመም ፣ ድካም ወይም ትክክለኛ የሆነ አካላዊ ምክንያት የሌለው ወይም በህክምና የማይድን የምግብ መንሸራሸር ችግር

ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ቢያንስ ለሁለት ሳምንት ያክል እራስዎት ላይ ካዩ እርዳታ መጠየቅ ይኖርብዎታል። በማንኛውም ጊዜ እራስዎን የመጉዳት ወይም ራስን የማጥፋት  ስሜት የሚሰማዎት ከሆነ በአስቸኳይ እርዳታ ያግኙ ።

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc

Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

ከደቡብ ኮርያ ጋር መዋሀድ አንፈልግም

Next Post

የሃገር ዉስጥ አጫጭር መረጃዎች

Related Posts

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ
Health

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ

June 15, 2026
38
በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው
Health

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው

June 4, 2026
24
⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ
Health

⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ

March 16, 2026
85
“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ
Health

“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ

February 17, 2026
48
ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ
Health

ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ

January 21, 2026
42
ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና
Health

ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና

August 25, 2025
89
Next Post
የሃገር ዉስጥ አጫጭር መረጃዎች

የሃገር ዉስጥ አጫጭር መረጃዎች

የስፖርት አጫጭር መረጃዎች

የስፖርት አጫጭር መረጃዎች

የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ድል

የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ድል

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?