አዲስ አበባ | ጥር 02፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ካስመዘገቡ ኢንቨስተሮች ጋር ተፈራረመ ::

ኮርፖሬሽኑ በመላው የኢንዱስትሪ ፖርኮች ግንባታን በማስፋፋት፤የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በማሳደግ፤ ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ፤ተተኪ ምርቶችን በማምረት ፤የአካባቢ ጥበቃ ሥራን በማጠናከር ከተሞችን ወደ ላቀ የዕድገት ደረጃ እንዲሸጋገሩ በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
ኢንቨስተሮቹ በ5 የተለያዩ ኢንዱስትሪ ፖርኮች ላይ ገብተው ለመስራት የሚያስችላቸውን የውል ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን በአግሮ ፕሮሰሲንግ፤በአልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣በመድሃኒት እንዲሁም በፕላስቲክ ማምረት ዘርፍ ይሰማራሉ ።
ኢንቨስተሮቹ በመቐለ ፤በጅማ እና በቦሌ ለሚ፣ በባህርዳር እና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ስራቸዉን የሚጀምሩ ሲሆን ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተፈራረሙ ባለሃብቶች 31ሺ ካሬ ሜትር የማምረቻ ሼድና 4.5 ሄክታር የለማ መሬት ተረክበው ወደ ስራ እንደሚገቡ ተገልጿል ።
በማህሌት ግርማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv












