አዲስ አበባ | ጥር 02፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የሁለተኛው ትውልድ አገራዊ ጥሪ ተከትሎ በሶስቱም ምዕራፎች ወደ አገር ለሚመጡ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን እንዲያውቁ የሚያደርጉ የኢትዮጵያን ብዝሀነት የሚያሳዩ ሁነቶች መዘጋጀታቸው ተገለፀ


ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የትውልድ መነጠልን ለማስቀረት ያግዛል የተባለው የሁለተኛው ትውልድ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።ይህንንም ተከትሎ በመጀመሪያው ምዕራፍ የሁለተኛው ትውልድ ጥሪ ወደ አገር እየገቡ የሚገኙ ዜጓች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልፆል።
የሁለተኛው ትውልድ አባላት አገራቸውን እንዲያውቁ ለማድረግ የሚያስችል መርሀ ግብሮች በአብይ ኮሚቴው ስለመዘጋጀቱ ነው የተገለፀው።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ ስለሺ ግርማ የኢትዮጵያ ሳምንት የኢትዮጵያን የምግብና መጠጦች ፣የእደ ጥበብ ውጤቶች፣ የሙዚቃ መሳሪያዎች እና ድምፀት የሚታዮበት ፣ የባህል አልባሳትና ባህልን የሚያሳዩ ፣የክልሎች የቱሪዝም ፀጋዎችን የሚተዋመቁበት፣
የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት የሚያሳይ የፐብሊክ ሌክቸር ፣ የጉብኝት መረሀ ግብር ፣የኢትዮጵያን ምርቶች የሚያሳይ ኤግዚቢሽን እና ባዛሮች፣ኢትዮጵያን እንዲያውቁ የሚያደርግ የግንዛቤ ማስጨበጫ መረሀ ግብሮች እና ኮንፍረንሶች ጭምር ተዘጋጅተዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሀመድ ኢድሪስ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሁለተኛው ትውልድ ጥሪን ተከትሎ ትውልዱ ወደ አገሩ እንዲገባ ለማድረግ በተለያዩ የአለም ክፍል በሚገኙ ሁሉም ኤምባሲዎች ትኩረት ተጥተው እየሰሩ ስለመሆኑ ገልፀዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv












