አዲስ አበባ | ጥር 02፤ 2016| NBC ETHIOPIA -በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ሚሽን [ዩኤንሶም] በኮንትራክት የያዘው ሄሊኮፕተር አስቸኳይ ሕክምና ለመስጠት በሄደበት የአቪየሽን ክስተት እንደገጠመው አረጋግጧል።

ኤኤፍፒ የዜና ወኪል የተባበሩት መንግሥታትን ሰነድ ተመልክቶ በሠራው ዘገባ ሄሊኮፕተሩ በገጠመው እክል ምክንያት ከዱሳምሬብ ደቡብ ምስራቅ 70 ኪሎ ሜትር አቅጣጫ አርፏል ብሏል።
የዜና ወኪሉ አክሎ በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች ሳይሆኑ ተቀጥረው የሚሠሩ ሶስተኛ ወገን ኮንትራክተሮች እንደነበሩ ዘግቧል።
ከተሳፋሪዎቹ መካከል አንዱ ሲገደል ሁለቱ ደግሞ አምልጠዋል በሄሊኮፕተሯ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ዜግነት እስካሁን ግልጽ አይደለም የበረራ ሠራተኞችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ናቸው። አብዛኛው ማዕከላዊ እና ደቡባዊ የሶማሊያ ክፍል በታጣቂው አል ሸባብ ቁጥጥር ሥር ነው የሚገኘው።
የጋልሙዱግ ክልል ፀጥታ ሚኒስትር መሐመድ አብዲ ሄሊኮፕተሩ በአል ሸባብ ቁጥጥር ሥር መዋሉን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
አልሻባብ ሶማሊያ ውስጥ በስፋት የሚንቀሳቀስ ታጣቂ ኢስላማዊ ቡድን ሲሆን፣ ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው ይነገራል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv












