አዲስ አበባ | ጥር 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ጤና ሚኒስቴር የጥር ወርን የጤናማ እናትነት ወር በሚል በመሰየም እናቶች ወደ ጤና ተቋማት ሄደው ክትትል እንዲያደርጉ የቅስቀሳ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማከናወን ጀመረ።
“ፍትሃዊ ተደራሽነት እና ጥራት ያለው የቅድመ ወሊድ ክትትል በወቅቱ በማስጀመር ጤናማ እናትነትን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል ነው የሚከበረው።
በየዓመቱ 10 ሺ እናቶች ከወሊድ ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ህይወታቸውን እንደሚያጡ እና አብዛኞቹ ምክንያቶችም መከላከል የሚቻሉ መሆናቸው ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በጉዳዩ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የገለጸው ሚኒስቴሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሁሉም አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በመቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/











