አዲስ አበባ | ጥር 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA – በቀጥታ ሥርጭት ላይ የነበሩ ጋዜጠኞችና ሌሎች የቴክኒክ ባለሙያዎች በታጣቂዎቹ የታገቱት ለአጭር ሰዓት ነው።

ማክሰኞ በቴሌቪዥን ስቱዲዮ በነበረው እገታና ጥቃት አንድ ጭምብል የለበሰ ታጣቂ ሽጉጥ በጋዜጠኛ ላይ ደቅኖ ይታይ ነበር። ሌላኛው ታጣቂ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ጣልቃ እንዳይገቡ ለማሳሰብ እፈልጋለሁ ቅረጹኝ እያለ ሲጠይቅ ነበር።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአገሪቱ እስር ቤቶች ውስጥ የአደገኛ እጽ አዘዋዋሪ አደገኛ ቦዘኔዎች አስነሱት በተባለ ነውጥ በርካቶች ተገድለዋል።
ኢኳዶር በደቡብ አሜሪካ የምትገኝና ፔሩና ኮሎምቢያን የምትጎራበት አገር ስትሆን ሕዝቧ 17 ሚሊዮን ይጠጋል።
ፕሬዝዳንቱ በኢኳዶር የአደገኛ እጽ ሰንሰለትን እበጣጥሳለሁ ብለው ቃል ገብተው ነበር በቅርብ ጊዜ ወደ ሥልጣን የመጡት።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/











