፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
አዲስ አበባ | ታህሳስ 30፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ኢትዮቴሌኮም ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃግብር አስጀመረ
35 ዓመታት የነፃ ልብ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከልን ለማገዝ የሚረዳ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ኢትዮቴሌኮም አዘጋጅቷል።
ኢትዮቴሌኮም ጥር ወርን የልብ ህሙማን ህፃናት ብሎ በመሰየም በቋሚነት በ6710 የአጭር የፅሁፍ መልዕክት በመጠቀም ለተቋሙ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡
በተጨማሪ ከ ጥር 1 እስከ ጥር 30 ኢትዮቴሌኮም በማህበራዊ ሚደያ የሚለቃቸውን ሀሳብ በመጋራት እና ለሌሎች በማጋራት እንዲሁም አዲስ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ-ገፅ ተጠቃሚ ሲሆኑ አንድ ሰው ከ30 እስከ 10 ብር ለልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል መለገስ የሚችልበትን አሰራር ዘርግቷል፡፡
መርጃ ማዕከሉ በዓመት ለ500 ታካሚዎች የነፃ የልብ ቀዶ ህክምና እየሰጠ ሲሆን አሁንም በርካታ ህፃናት ህክምናውን እየጠበቁ ናቸው።
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv