አዲስ አበባ | ታህሳስ 29፤ 2016| NBC ETHIOPIA – በሰሜን ምዕራብ ናይጀሪያ በካዱና ግዛት ሶስት መንደሮች በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 17 ሰዎች ሲገደሉ 58 የሚሆኑ ታፍነው መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

እሁድ እለት በካሩ ወረዳ ታጣቂዎች ያደረሱትን ጥቃት የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል ፡፡
ናይጀሪያ በተለያዩ ጊዚያት በሀገሪቱ ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየተበራከቱ መምጣታቸውን፤ ለዚህም ተጠያቂ የሚሆነው የአሸባሪው ቦኮሃራምና የምዕራብ አፍሪካ እስላማዊ መንግስት ቡድን እንደሆነ ተገልጿል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












