አዲስ አበባ | ታህሳስ 25፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የገና በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፋለች።

ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ አምላክ ከሰው ልጆች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ ሰማይን እና ምድርን ለማስታረቅ እንደ ሰው ስጋን ለብሷል ብለዋል በዓሉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ።
በመሆኑም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ሲከበር ከራስ ወዳድነት በወጣ፣ የተራቡ የታረዙና የተጠሙ በሚታሰቡበት፣ የተበደሉ የታመሙና የተፈናቀሉ የሚታወሱበት እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ውስጥ ለገቡ ወገኖች አለኝታ በመሆን መከበር ይገባዋል ብለዋል።
“ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ እግዚአብሔር መፍትሄ ይሰጠን ዘንድ በፀሎት እንትጋ” ሲሉ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ መልዕከታቸውን አስተላልፈዋል።
በመቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












