አዲስ አበባ | ታህሳስ 24፤ 2016| NBC ETHIOPIA -በጃፓን መዲና ቶኪዮ በሚገኘው ሃኔዳ አየር ማረፊያ ሁለት አውሮፕላኖች ተጋጭተው አምስት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ፡፡

በግዙፉ ኤየርባስ ኤ350 የመንገደኞች አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ 379 ሰዎች ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው ከአደጋው ማምለጥ የቻሉ ሲሆን በአስተኛው አውሮፕላን ተሳፍረው ከነበሩት ስድስት ሰዎች መካከል ግን አምስቱ ሕይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧ፡፡
የመንገደኞች አውሮፕላኑን በሙሉ በሙሉ በእሳት ከመያያዙ በፊት ተሳፋሪዎች እና የበረራ አስተናጋጆች በአደጋ ጊዜ መውጫ በኩል አምልጠዋል።
የጃፓን ባለስልጣናት እንደገለጹት በአነስተኛው አውሮፕላን ተሳፍረው የነበሩት በሀገሪቱ በተከሰተው ሱናሚ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የአደጋ ጊዜ ቁሳ ቁስ ጭነው ለመብረር ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአነስተኛው አውሮፕላን አብራሪ ከአደጋው ቢተርፍም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት እየተገለጸ ነው፡፡
አደጋውን ተከትሎ ወደ ቶኪዮ ሃኔዳ አየር ማረፊያ የሚደረጉ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን አንዳንዶቹ አቅጣጫቸውን ወደሌሎች አየር ማረፊያዎች እንዲቀይሩ ተደርጓል።
ኤየርባስ ኤ350 አውሮፕላን ትልቅ የሚባል አደጋ ሲያጋጥመው ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












