Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

ኮሌራ(Cholera) ምንድን ነው?

December 29, 2023
in Health
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ታህሳስ 19፤ 2016| NBC ETHIOPIA-ኮሌራ ቪብሪዮ ኮሌራ በሚባል መርዛማ ባክቴሪያ የሚመጣ የአንጀት ኢንፌክሽን ሲሆን አጣዳፊ ተቅማጥ ያስከትላል።

በአለም ዙሪያ ከ1.3 እስከ 4 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች በየአመቱ በኮሌራ ይያዛሉ ። ከ21,000 እስከ 143,000 የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ በዚህ በሽታ ይሞታሉ።

ኮሌራ እንዴት ይተላለፋል?

ኮሌራ የሚተላለፈው በኮሌራ ባክቴሪያ የተበከለ ውሃ ስንጠጣ ወይም ምግብ ስንመገብ ሲሆን ይህም የሚከሰተው የምንጠቀመው ውሃና ምግብ በበሽታው በተያዘ ሰው ሰገራ ሲበከል ነው።

ኮሌራ የውሃ እጥረት እና የንፅህና ጉድለት ባለባቸው ቦታዎች የመከሰቱና የመዛመት እድሉ ሰፊ ነው።

የኮሌራ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የኮሌራ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ቀለል ያሉ ምልክቶች ያሳያሉ ወይም ምንም ምልክት አይኖራቸውም። በግምት ኮሌራ ከያዛቸው 10 ሰዎች ውስጥ አንዱ ከባድ ምልክት ያሳያል። አንድ ሰው የተበከለ ምግብ ከበላ ወይም ውኃ ከጠጣ በኋላ ምልክቶቹን ለማሳየት ከ12 ሰዓት እስከ 5 ቀናት ይፈጅበታል።

ምልክቶቹም፦

-በዋናነት ተቅማጥ እና ማስመለስ ሲሆኑ ከባድ የሆነ የኮሌራ ህመም የያዛቸው ሰዎች መጥፎ ጠረን ያለውና የ”ሩዝ ውሃ” የመሰለ ተቅማጥ ይኖራቸዋል።

-ተቅማጥና ትውከቱ ቀጣይነት ያለው ከሆነ ደግሞ ከፍተኛ የሰውነት ፈሳሽ መሟጠጥ፣ ፈጣን የልብ ምት፣ ዝቅተኛ የደም ግፊት፣ከዚህም ጋር ተያይዞ የኩላሊት መጎዳት፣ ገፋ ሲል ሞት ያስከትላል።

-አልፎ አልፎ የሆድ ቁርጠት ቢኖራቸውም ብዙዎቹ በኮሌራ የተያዙ ሰዎች ትኩሳት አይታይባቸውም።

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

Cholera – Diagnosis on Medical Report. Composition of Medicaments. Cholera, Medical Concept with Selective Focus. Toned Image. 3D.

-ኮሌራ በልጆችም ሆነ በአዋቂዎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከመሆኑም በላይ በበሽታው ተይዘው ከፍተኛ ተቅማጥ ያላቸውን ሰዎች ሕክምና ካልተደረገላቸው በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ሊገድል ይችላል። ነገር ግን ቶሎ ሕክምና ሲደረግላቸው አብዛኛውን ጊዜ ዘላቂ ጉዳት ሳያስከትልባቸው ያገግማሉ።

-የኮሌራ ዋነኛው ህክምና የሰውነትን ፈሳሽ መተካት ነው። ይህም በORS(ኦራኤስ) ወይም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በደም ስር በሚሰጡ ፈሳሾች ይከናወናል።

– ከባድ ምልክት ላላቸው ሰዎች ፀረ-ባክቴርያ መድሀኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ።

– ከ 5 አመት በታች ላሉ ህፃናት የዚንክ እንክብል ይሰጣቸዋል። ይህም የበሽታውን ጊዜ ለማሳጠር እና ከሌሎች የተቅማጥ በሽታዎች ለመከላከል ይጠቅማቸዋል።

-የኮሌራ ሕሙማን አብዛኛውን ጊዜ ከሕመማቸው ካገገሙ በኋላ የኮሌራ ባክቴሪያ ተሸካሚዎች ባይሆኑም እንደገና ከተጋለጡ ይታመማሉ።

ኮሌራን እንዴት መከላከል ይችላሉ?

-እጅዎን ምግብ ከማብሰልዎ በፊት፣ ልጆችዎን ከመመገብዎ በፊት፣ ሽንት ቤት ከተጠቀሙ በኋላ (ወይም ልጅዎን ሽንት ቤት አስጠቅመው ካጸዳዱ በኋላ) ፣ የታመመን ሰው ከተንከባከቡ እና/ወይም ከነኩ በኋላ በሳሙና እና በንፁህ ውሃ ይታጠቡ።

-ንጹህ ውሃ መጠጣት እና መጠቀምዎን ያረጋግጡ።

-ውሃዎ ደህንነቱ የተጠበቀ ላይሆን ይችላል ብለው የሚያስቡ ከሆነ በውሃ ማከምያ ኬሚካሎች አክመው ይጠቀሙ።

-ምግብን በደንብ ያብስሉ፣ ይሸፍኑ ፣ በትኩሱ ይመገቡ፣ ያልበሰሉ ምግቦችን አይመገቡ።

-የውሃ ማከሚያ ምርት ከሌለ ማፍላት ውሃን አስተማማኝ ለማድረግ ውጤታማ መንገድ ነው።

-ከቧንቧ የሚወጣ ውሃ እና በከረጢት የሚሸጡት በረዶዎች የተበከሉ ሊሆን ስለሚችሉ አክሞ መጠቀም ወይም ፈፅሞ አለመጠቀም።

የሽንት ቤት ንፅህናን መጠበቅ ፣ ባክቴሪያው እንዳይሰራጭ ለመከላከል ከታመሙ እና ከሌሎች ሰዎች የሚወጣው የሽንት ቤት ፍሳሽና ቆሻሻ አካባቢን፣ ውኃንና ምግብን እንዳይበክል በጥንቃቄ ማስወገድ።

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/

Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

የስፖርት አጫጭር መረጃዎች

Next Post

በፈረንጆቹ 2023 ህይወታቸውን ያጡ ታዋቂ የፊልም ተዋንያን

Related Posts

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ
Health

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ

June 15, 2026
38
በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው
Health

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው

June 4, 2026
24
⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ
Health

⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ

March 16, 2026
85
“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ
Health

“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ

February 17, 2026
48
ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ
Health

ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ

January 21, 2026
42
ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና
Health

ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና

August 25, 2025
89
Next Post
በፈረንጆቹ 2023 ህይወታቸውን ያጡ ታዋቂ የፊልም ተዋንያን

በፈረንጆቹ 2023 ህይወታቸውን ያጡ ታዋቂ የፊልም ተዋንያን

የሰቆጣ ቃል ኪዳን የአፈፃፀም ግምገማ እና የዕቅድ ማፅደቂያ ውይይት እየተካሄደ ነው

የሰቆጣ ቃል ኪዳን የአፈፃፀም ግምገማ እና የዕቅድ ማፅደቂያ ውይይት እየተካሄደ ነው

የጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ

የጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?