አዲስ አበባ | ታህሳስ 18፤ 2016| NBC ETHIOPIA- በትግራይ ክልል ከዉቅሮ 11 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘዉ በአፍሪካ የመጀመርያዉ መስጊድ ስለመሆኑ የሚነገርለት ታሪካዊዉ አልነጃሺ መስጊድ በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል ተከስቶ በነበረዉ ጦርነት ጉዳት እንደደረሰበት ይታወቃል። ታሪካዊዉ አልነጃሺ መስጊድ በትግራይ በተካሄደዉ ጦርነት ጉዳት እንደደረሰበት መስማቱም ብዙዎችን አሳዝኖአል።


ይህንን ታሪካዊ ቦታ ወደ ቀድሞ ገፅታዉ ለመመለስ ብሎም መሠረተ ልማቶች ተሟልተዉለት ለእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ለጎብኝዎች ምቹ እንዲሆን ለማድረግ የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።
አልነጃሺን እንዲሁም ሌሎች ጥቃት የደረሰባቸዉን ተቋማት መልሶ አገልግሎት ላይ ለማዋልና የክልሉን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ወደ ቀድሞ ለመመለስ የቱሪዝም ሚኒስቴር ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን በይፋ አስጀምሯል።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












