አዲስ አበባ | ታህሳስ 18፤ 2016| NBC ETHIOPIA- አማራ ባንክ ሁለተኛ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ የባንኩ የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በበጀት አመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉ ተገልጿል፡


በፈጣን እና ቀልጣፋ የዲጂታል ባንኪንግ መተግበሪያ አማካኝነት በርካታ ተጠቃሚዎችን ማፍራት የቻለ ሲሆን ተጨማሪ 125 የኤቲኤም ማሽኖችን አገልግሎት ላይ አውሏል፡፡
የግብርናውን ዘርፍ ለመደገፍ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የተነገረው ባንኩ ከሰጠው ብድር በተጨማሪ ባህላዊ የግብርና ስርዓትን ለማዘመን ለገበሬዎች 222 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ትራክተሮችን ገዝቶ አስረክቧል፡፡
አማራ ባንክ በበጀት አመቱ ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘት እንደተቻለ ተገልጿል።
የቅርንጫፎቹ ብዛት ከ290 የተሻገረው ባንኩ ተቀማጭ ገንዘቡ 19.8 ቢሊዮን በላይ የደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ሀብቱን 28.4 ቢሊዮን ብር ተሻግሯል፡፡
በሀይማኖት ወርቁ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












