አዲስ አበባ | ታህሳስ 18፤ 2016| NBC ETHIOPIA- ሊጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ 2023 በዓለም ላይ ደስተኛ የሆኑ ዜጎቸ የሚኖሩባቸው ሀገሮች ማን እንደሆኑ ያውቃሉ?
በአለም ደስተኛ የሆኑት ዜጎቸ የሚኖሩባቸው ሀገራት 5ቱን ከታች ዘርዝረናቸዋል
1.ፊንላንድ (Finland)

በ2023 የዓለም ደስታ ሪፖርት መሰረት ፊንላንድ በዓለም አንደኛ ደስተኛ ከሚባሉ ሀገራት መካከል ። ሀገሪቱ እጅግ ደስተኛ በመሆን በተከታታይ ስድስት ዓመት አንደኛ በመሆን ቀጥላለች ፡፡
2. ዴንማርክ (Denmark)

ዴንማርክ በዓለም ላይ ሁለተኛዋ ደስተኛ ሀገር ስትሆን የዓለም ደስታ ሪፖርት 7.586 ነጥብ አስመዝግባለች፡፡ ዴንማርክ በዓለም ሁለተኛዋ ደስተኛ አገር ስትሆን በተከታታይ አራተኛ ዓመት ሆኗታል።
3. አይስላንድ (Iceland)

እ.ኤ.አ. በ2023 በዓለም ሶስተኛዋ ደስተኛ ሀገር አይስላንድ ስትሆን በዓለም የደስታ ዘገባ መሰረት 7.530 ነጥብ አግኝታለች። አይስላንድ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ በተከታታይ ሁለተኛ ዓመት ሆኗታል። አይስላንድ በሕዝብ ብዛት በዚህ ዝርዝር ውስጥ ትንሿ ሀገር ስትሆን በደሴቲቱ 375,436 ብቻ ህዝብ ይኖራሉ።
4. እስራኤል (Israel)

በ2023 እ.ኤ.አ. እስራኤል 7.473 በማስመዝገብ ከዓለም አራተኛዋ ደስተኛ ሀገር ነች።
ከእ.ኤ.አ. ከ2022 የዓለም የደስታ ሪፖርት እትም ሀገሪቱ ከዘጠነኛ ወደ አራተኛ ከፍ ብላለች።
5. ኔዘርላንድ (Netherlands)

በዓለም የደስታ ሪፖርት መሰረት ሆላንድ 7.403 በማስመዝገብ በዓለም አምስተኛ ደስተኛ ሀገር ተብላለች።












