አዲስ አበባ | ታህሳስ 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA – በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በምትገኘው ሞ ከተማ አራት ልጆቹን እና ባለቤቱን በመግደል የተጠረጠረው የ33 ዓመት ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ወንጀሉን በተመለከተ ለፖሊስ ጥቆማ የደረሰው አንዲት ጎረቤት የቤተሰቡን አባላት ለማግኘት ያደረገችው ተደጋጋሚ ጥረት ሳይሳካ ቀርቶ የቤቱ በር እጀታ ላይ ደም ካየች በኋላ ነው።
ፖሊስ ወንጀሉ በተፈጸመበት ቦታ ሲደርስ ከአባት ውጭ ሁሉም የቤተሰብ አባላት በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፎ ማግኘቱን ገልጿል። ህይወታቸው ይለፉት ልጆች ዕድሜ ከ9 ወር እስከ 10 ዓመት መካከል ያሉ ናቸው፡፡
ከዚያም የደኅንነት መከታተያ ካሜራዎችን በመከተል ተጠርጣሪውን ከከተማዋ ርቆ በሚገኝ ከተማ በወላጅ አባቱ መኖሪያ ቤት በቁጥጥር ስር አውሎታል።

ዐቃቤ ሕጉ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተጠርጣሪው ከዚህ ቀደም በወንጀል ተከሶ ባያውቅም የቤት ውስጥ ጥቃት በመፈጸም በፖሊስ ይታወቃል ያሉ ሲሆን እኤ.አ 2019 ላይ ግለሰቡ ባለቤቱን በስለት አጥቅቶ ነበር ግለሰቡ ክስ ሳይመሰረትበት የቀረው ባለቤቱ ክስ ባለመመስረቷ እንዲሁም በወቅቱ የአእምሮ ጤና እክል ስለነበረበት ነው ተብሏል።
ዐቃቤ ሕጉ እናት እንዲሁም የ10 እና የ7 ዓመት ሴት ልጆች በርካታ ቦታ በስለት ተወግተው መደገላቸውን ተናግረው ሁለቱ የአራት እና የ9 ወር ልጆች ግን አካላቸው ላይ የሚታይ ጉዳት የለም ብለዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












