አዲስ አበባ | ታህሳስ 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA የነብዩ መሐመድ ልደት የሚዘከርበት የመውሊድ በዓል በአለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ውይይቱ “የመውሊድ አከባበር ባህላዊ መልኮች” በሚል እየተካሄደ ነው፡፡


መውሊድ በተለያዩ የዓለም አገራት የሚከበር ቢሆንም በኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ ይከበራል፡፡
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተለያየ የአከባበር መልክ ያለው የመውሊድ በዓል በአለም አቀፉ የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዩኒስኮ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ ሊደረግ እንደሚገባ በውይይት መድረኩ ተመላክቷል።
በኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ በተዘጋጀው በዚህ ውይይት የመውሊድ አከባበርን የተመለከቱ ጥናቶች ሊደረጉ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ ኃላፊዎቸ፣ የእስልምና ሃይማኖት አባቶች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












