አዲስ አበባ | ታህሳስ 16፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ከግለሰቦችና ከተቋማት ጋረ በመሆን ለ 12 ተከታታይ ክፍሎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዉይይት ሲያደርግ የቆየዉ የሀሳብ መዋጮ መድረክ የምዕራፍ አንድ የማጠቃለያ መርኃ-ግብር በዛሬዉ ዕለት እየተካሄደ ይገኛል።


በጎና መልካም እሴትን ለመገንባት ያለመዉ መድረክ በ 12 ተከታታይ ክፍሎች ያነሳቸዉ ሀሳቦች በማጠቃለያ መርኃ-ግብሩ ላይ የታወሱ ሲሆን ሀሳቦቹ ምን ያህል ተደራሽ እንደሆኑ እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዮች አንፃር ግምገማ ተደርጎባቸዋል።
ባለፉት መድረኮች የተስተዋሉ ድክመቶችና ክፍተቶች እንዲሁ ተጠቅሰዋል። በቀጣይ መነሳት ያሉባቸዉን ጉዳዮች ጨምሮ በምን መልኩ መቀጠል አለበት በሚለዉ ላይ ተሳታፊዎች ዉይይት አድርገዋል።
የሀሳብ መዋጮ መድረክ የመንግስት ተቋማትን፣ ምሁራንን፣ የሀይማኖት አባቶችን፣ የሲቪክ ማህበራትንና ሁሉንም አካላት ያሳተፈ እንደነበር ተገልጿል።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












