አዲስ አበባ | ታህሳስ 16፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የታጠቁ ቡድኖች በማዕከላዊ ናይጀሪያ በምትገኘው ፕላቲዩ በተባለች ግዛት በከፈቱት ተኩስ ከሶስት መቶ በላይ ንጹሀንን ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የናይጀሪያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ታጣቂዎቹ የተኩስ እሩምታ በመክፍት ከመቶ በላይ ሰዎችን መግደላቸው እንዲሁም የተፈጸመው ጥቃት ሀይማኖትና ጎሳን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ባለስልጣናቱ ገልጸዋል፡፡
በአካባበቢው የነበሩ የአይን እማኞች እንደሚሉት ሽፍቶቹ ሀይማኖትና ጎሳን እየመረጡ ጥቃት እንደሚያደርሱ ነው፡፡ ይህም በጎሳዎች መካካል ውጥረት እንዲፈጠር ምክንት ይሆናል እየተባለ ነው፡፡ ጥቃት ፈጻሚዎቹ በደንብ የተደራጁ ቡድኖች በመሆናቸው መንግስት ጉዳዩን በትኩረት እንዲከታተለው በስፍራው የሚገኙ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
እስካሁን ድረስ ለጥቃቱ ሀላፊነት የወሰደ አካል አለመኖሩም ታውቋል፡፡ የፕላቲዩ ግዛት በማዕከላዊ ናጀሪያ የምትገኝ በግብርና የሚተዳደሩ የተለያየ ሀይማኖትና ጎሳ የሚኖርባት ስትሆን ብዙ ጊዜ በሙስሊምና ክርስቲኖች መካካል ግጭት ይፈጠርባታል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት