አዲስ አበባ | ታህሳስ 12 ፤ 2016 -በአይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ የሚመክር መድረክ እየተካሄደ ነው።


መድረኩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ ነው።
በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውጤታማ እንዳይሆኑ በዋነኝነት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ፈተና እንደሆኑበት ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ120 በላይ ኢንቨስተሮች ስራ ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ቻይና፣ ህንድ እና የአውሮፓ ሀገራት ዋነኞቹ ኢንቨስተሮች ናቸው።
ኮርፖሬሽኑ በተመሳሳይ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችንም ለመሳብ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።


መድረኩ ከእዚህ በኋላ ቢያንስ በአመት ሁለት ጊዜ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ2030 በአፍሪካ ቀዳሚው ለመሆን ውጥን ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ተነግሯል።
በመድረኩ የተለያዩ ሚኒስትሮች፣ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ተቋማት ሀላፊዎችና ባለሀብቶች ተሳታፊ ሆነውበታል።
በመቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv