አዲስ አበባ | ታህሳስ 12 ፤ 2016 – የቀድሞው ትዊተር በአሁን መጠሪያው ኤክስ የተሰኘው ማህበራዊ ሚድያ በመላው ዓለም ለአንድ ሰዓት ያህል ተቋረጠ።

ማህበራዊ ሚድያዎች ሲቋረጡ መዝግቦ የሚያስቀምጠው ዳውንዲቴክተር (Downdetector.com) በአሜሪካ ብቻ 47 ሺህ ያክል የኤክስ እና የኤክስ ፕሮ ተጠቃሚዎች መጠቀም አቅቷቸው ነበር ብሏል።
በእንግሊዝ እና በእስያ ያሉ የተወሰኑ ተጠቃሚዎችም እንዲሁ ኤክስ ላይ የተለጠፉ ይዘቶችን ማግኘት ሳይችሉ ቆይቷል።
ኤክስ ተቋርጦ በነበረ ሰዓት ወደ ማህበራዊ ሚድያው የተጠቀሙ ተጠቃሚዎች “እንኳን ወደ ኤክስ መጡ” (“Welcome to X!”) የሚል መልዕክት ብቻ ነበር የሚታያቸው።
ኤክስ መሥራት ባቆመ በደቂቃዎች ውስጥ #TwitterDown የተሰኘው ሃሽታግ በብዙዎች ዘንድ ተጋርቷ ነበር ነገር ግን ኤክስ ከአንድ ሰዓት ቆይታ በኋላ ወደ ቀድሞ ሥራው ተመልሶ ተጠቃሚዎች ማህበራዊ ሚድያውን ድጋሚ ማግኘት እንደቻሉ ቢቢሲ ገልጿል።
ኢላን መስክ ባለፈው ዓመት ነው የቀድሞውን ትዊተር በ44 ቢሊዮን ዶላር ገዝቶ የግል ንብረቱ እንዳደረገው የሚታወስ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት