አዲስ አበባ |ታህሳስ 04፤ 2016| NBC ETHIOPIA – 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ እንደሚያካሂድ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምክር ቤቱ ከሚቀርቡ አጀንዳዎች መካከል የ3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ የሚያጽድቅ ሲሆን፤ ከዚህ በመቀጠል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በሊባኖስ መንግስት መካከል በሥራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ በሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረቡ ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳቦች መርምሮ አዋጆቹን ያጽዳቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በፓኪስታን መንግሥት መካከል የተፈረመውን የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት መካከል የተደረገውን በሁለትዮሽ ወታደራዊ ቴክኒካዊ ትብብር ወቅት የተገኙ የፈጠራ ሥራ ውጤቶች እና ንብረቶች የጋራ ጥበቃ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












