ሳፋሪኮም ‘ተረክ በM- PESA’ የተባለ ደንበኞቹን እና አከፋፋዮቹን የሚሸልምበት የ 3 ወራት መርሐግብር አስጀምሯል።

የመክፈቻዉ መርሐግብር ስነስርዓት በዛሬዉ ዕለት የተካሄደ ሲሆን በሽልማት መልክ የቀረቡ 4 መኪኖች፣ 24 ባጃጆች እንዲሁም ከ 2000 በላይ የሆኑ ስልኮች ለባለዕድለኞች እንደተዘጋጁ ተገልጿል።
ደንበኞች፣ አከፋፋዮችና ኤጀንቶች አሸናፊ ለመሆን ማድረግ ያሉባቸዉ ሂደቶች የተቀመጡ ሲሆን ሂደቶቹ በመክፈቻ ስነስርዓቱ በዝርዝር ተገልፀዋል።
የሽልማት መርሐግብሩ ለሶስት ወራት ይቆያል በዚህም በየሳምንቱና በየወሩ ሽልማቶቹ ለአሸናፊዎች እንዲደርሱ ይደረጋል ተብሏል።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












