አዲስ አበባ | ህዳር 28፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ኢትዮ ቴሌኮም ዲጅታል አሰራርን ለማጠናከር ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ከሸገር ከተማ ጋር ስምምነት አድርጓል፡፡


ከኦሮሚያ ክልል የተደረገው ስምምነት ክልሉ ዲጅታል አሰራርን በትምህርት ፣ በጤና፣ በግብርና ፣በመሬት አስተዳደር፣ በትራንስፖርት እና መሰል ዘርፎች ለማጠናከር ያግዛል ተብሏል ።
ከሸገር ከተማ አስተዳደር እንዲሁ አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ያስችላል ተብሎለታል።


የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ይህ ስምምነት ሀገራችን በተለያዩ የአገልግሎ ዘርፎች ዲጅታል አሰራርን ለማዘመን ኢትዮ ቴሌኮም ቴክኖሎጂ የሚያቀርብበት ነው፤ በመንግስትና በዜጎች መካከል ያለውን መስተጋብርም ያጠናክራል ብለዋል።
በአጠቃላይ ስምምነቱ አገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምኑ የዲጅታል መሰረተ ልማቶችን በማቅረብ እንግልትን እንደሚቀንስ ተገልጿል።
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv












