አዲስ አበባ | ህዳር 27፤ 2016| NBC ETHIOPIA-በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው የቡና ፈንገስ የቡና ምርትን በእጅጉ ሲጎዳ ቆይቷል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከከፋ ባዮ ኮንትሮል አግሮ ኢንዱስትሪ እና ሌሎች የአፍሪካ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ችግሩን ለመቅረፍ ምርምሮች ሲያደርግ ቆይቷል።

በዛሬው ዕለትም የምርምሩን ግኝት ይፋ አድርጓል። የምርምር ውጤቱ የቡና ፈንገስን ከ70% በላይ እንደሚከላከል የተገለጸ ሲሆን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና አየር ንብረት ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
በተጨማሪም ቡና ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንደመሆኑ ችግሩን ቀርፎ የሚያመጣውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተነግሯል።
ግኝቱ ከኢትዮጵያ ባሻገር የአፍሪካን የቡና ዘርፍ የሚያድን ነው የተባለ ሲሆን ዘርፉን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት አንድ ደረጃ ወደፊት የሚያራምድ ነው ተብሎለታል።

በግኝቱ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ቀዳሚ የቡና አምራች እንደመሆኗ የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ምርቱን በተመለከተ ለሚገጥሙ ችግሮች መፍትሄ የማፈላለግ ትልቅ ሃላፊነት እንዳለባት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ ገልጸዋል።
በእዚህም መሰረት ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ተነስቷል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












