አዲስ አበባ | ህዳር 24፤ 2016| NBC ETHIOPIA – እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ የኒክ ፖፕን ግልጋሎት የማያገኘው ኒውካስል ዩናይትድ ዴቪድ ዴ ሂያን ለማዘዋወር ማሰቡ ተሰምቷል።

የ31 አመቱ እንግሊዛዊ በ14ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድን አንድ ለምንም በረቱበት ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት አቋርጦ ለመውጣት መገደዱ ይታወሳል።
ኒክ ፖፕ ከደረሰበት የትክሻ ስብራት ያገግም ዘንድ የአምስት ወራት ጊዜ እንደሚፈጅበትና እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ወደ ሜዳ እንደማይመለስ ተገልጿል።
ጀርመን የምታሰናዳው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ሊያመልጠው ይችላል ተብሏል።
እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ፣ ማግፓይሶች የእርሱን ክፍተት ለመሙላት የቀድሞውን የማንችስተር ዩናይትድ የግብ ዘብ ዴቪድ ዴ ሂያ የማዘዋወር እቅድ አላቸው።
ዴ ሂያ በ2022-23 የውድድር አመት መጨረሻ ላይ ከኦልትራፎርዱ ክለብ ከተሰናበተ በኋላ ኢንተር ሚያሚና አል- ናስርን ጨምሮ ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ተያይዞ ቢነሳም እስካሁንድረስ ማረፊያው አልተለየም።
ስፔናዊው የግብ ዘብ እረጅሙን የእግር ኳስ ህይወቱን ወደ አሳለፈበት ፕሪሚየር ሊግ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












