አዲስ አበባ | ህዳር 21፤ 2016| NBC ETHIOPIA – “የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ ኤችአይቪ መከላከል” በሚል መሪ ቃል የዓለም የኤድስ ቀን ተከበረ ። የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ጨምሮ በርካታ የጤና ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

እ.ኤ.አ በ2022 በዓለም አቀፍ ደረጃ 39 ሚሊዮን ሰዎች ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ሲሆን፤ 630,000 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ያጣሉ። በዚሁ ዓመት 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በኤችአይቪ የተያዙ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
በሀገራችን የኤችአይቪ የስርጭት ምጣኔ 0.91% ሲሆን በዚህም ስሌት 610,350 በላይ የሚሆኑ ወገኖች ኤችአይቪ በደማቸው እንደሚገኝ መረጃዎች ያሣያሉ። ከ8,257 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ የሚኖር ሲሆን 11,322 የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በኤች አይ ቪ ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ።
አሁን ላይ በአለም አቀፍ ደረጃም እንደ ሃገርም ብዙ ትኩረታችን ወደ ሌላ አቅጣጫ ሚስቡ ጉዳዩች ቢኖሩም ኤችአይቪ መጥፋቱን እና ስርጭቱ የለም ሚለዉን ማሣያ ግን አይደሉም። አሁንም ትኩረትን እንደሚሻና ሁላችንም ልብ ልንለዉ የሚገባ ጉዳይ እንደሆነም በመድረኩ ተነስቷል።
በአስናቀች መላኩ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












