አዲስ አበባ | ህዳር 21፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የኤችኤይቪ ቫይረስ ሥርጭትን የሚገታው በሙከራ ላይ የነበረው ፒአርኢፒ የተባለው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ።

የመድኃኒቱ ውጤታማነት የተረጋገጠው በመላው እንግሊዝ ከተወጣጡ እና በጥናቱ በተካተቱ ከ24 ሺህ በላይ የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ላይ ምርመራ ከተካሄደ በኋላ ነው።
በእንግሊዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፒአርኢፒ የተሰኘውን ይህን መድኃኒት ከሥነ ተዋልዶ ጤና ክሊኒኮች ጋር እየወሰዱ ይገኛሉ።
ጥናቱ ከአውሮፓውያኑ ጥቅምት 2017 እስከ ሐምሌ 2020 ባሉት ጊዜያት እንግሊዝ ውስጥ በሚገኙ 157 የሥነ ተዋልዶ ጤና ተቋማት ላይ ተካሂዷል።
ይህ ጥናት ‘ፕሪ ኤክስፖዠር ፕሮፍላክሲስ (ፒአርኢፒ)’ የተባለው መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን መድኃኒቱ በኤችአይቪ የመያዝ ዕድልን በ86 በመቶ ይቀንሳል።
ፒአርኢፒ ቀደም ብሎ የነበሩትን ቴኖፎቪር ዲሶፕሮክሲል እና ኢምትሪሳይታቢን የተባሉ የኤችአይቪ መድኃኒቶችን የያዘ ሲሆን፣ የኤችአይቪ ቫይረስ ወደ ሰውነት እንዳይገባ እና በሰውነት ውስጥ ከገባም በኋላ ራሱን እንዳያባዛ የሚያድርግ ሲሆን መድኃኒቱ በክኒን መልክ በቀን አንዴ መወሰድ ወይም ከወሲብ ግንኙነት ቀደም ብሎ መውሰድ እንደሚቻል ቢቢሲ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA












