አዲስ አበባ | ህዳር 7፤ 2016| NBC ETHIOPIA የጤና ሚኒስቴር አርቲስት መቅደስ ጸጋዬን የኢትዮጵያ ጨቅላ ህጻናት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።

እለቱ ”ለሁሉም ጨቅላ ህጻናት እንደተወለዱ የገላ ለገላ እንክብካቤ ፤ በቀላል ጥረት ፤ትልቅ ዉጤት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ነው እየተከበረ የሚገኘው።
በኢትዩጵያ ያለግዜ የተወለዱ ጨቅላ ህጻናት ለመደገፍ በሚደረጉ የግንዛቤ ስራዎች፥ የጤና ሚኒስቴር አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ የኢትዮጵያ ጨቅላ ህጻናት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።
በመድረኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓመት 15 ሚሊየን ጨቅላ ህጻናት ያለቀናቸው እንደሚወለዱ ተገልጿል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣የክልል ጤና ቢሮ ሀላፊዎች ፣ የአጋር ድርጅቶች፣ ባለድርሻ አካላት እና የክብር አንግዶች ተገኝተዋል።
በሰላማዊት ወንድወሰን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv