አዲስ አበባ | ህዳር 05 2016| NBC ETHIOPIA – የፌደራል የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የዘንድሮውን የፀረ ሙስና ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የዘንድሮ 20ኛው የፀረ ሙስና ቀን ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው ፤ በህብረት እንታገል በሚል መሪ ቃል ይከበራል። ቀኑም በተለያዩ ሁነቶች ከህዳር 1 እስከ ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጧል፡፡

የፀረ ሙስና ቀኑን ከማክበር ባሻገር የተቋማት አመራሮች እና የስራ ኃላፊዎች ሀብታቸውንና የገቢ ምንጫቸውን በማሳወቅና በማስመዝገብ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ይሰራል ተብላል፡፡
እንደ ሀገር የፀረ ሙስና ትግል እና እንቅስቃሴ ቢደረግም አሁንም ለአገሪቷ ትልቅ ስጋት በመሆኑ በጉዳዩ ላይ የሚታዩ ችግሮች በመለየት መፍትሄዎቻቸዉን ለማንፀባረቅ ንቅናቄው እንደሚያግዝ በመግለጫው ተነስቷል፡፡
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












