አዲስ አበባ | ጥቅምት 21፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ቦቢ ቻርልተን የቀብር ስነ ስርዓት በፈረንጆች ህዳር 13 እንደሚፈጸም ታውቋል።

ክለቡ እንዳስታወቀው፣ የቀብር ስነ ስርዓቱ በማንችስተር ካቴዴራል ይፈጸማል።
አስከሬኑ የቀብር ስፍራው ከመድረሱ በፊት ኦልትራፎርድ ስታዲዮም አርፎ በደጋፊዎች የክብር ሽኝት እንደሚደረግለት አክሏል።
እንግሊዛዊው የአለም ዋንጫ አሸናፊ ከ10 ቀናት በፊት በ86 አመቱ እንዳረፈ ይታወሳል።
የኦልትራፎርዱ ክለብ ደጋፊዎች ዕሁድ እለት በማንችስተር ደርቢ ጨዋታ ሊያሰሙት የነበረውን የጸረ- ግሌዘር ተቃውሟቸው ለቀድሞ ባለውለታቸው ክብር ሲሉ ሰርዘዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












