አዲስ አበባ | ጥቅምት 20 2016| NBC ETHIOPIA -ቼልሲ በ2013 ዊሊያንና ሳሙኤል ኤቶን ሲያዘዋውር የፋይናንስ ህጉን መተላለፍ አለመተላለፉ?፣ ምርመራ እየተደረገበት ነው።

ክለቡ ከ2012 – 2019 ባሉት አመታት ያልተሟሉ የፋይናንስ መረጃዎችን ማስገባቱ ከተረጋገጠ በኋላ በሳለፍነው ሃምሌ ወር የ8.6 ሚሊዮን ፓውንድ ቅጣት እንደተጣለበት ይታወሳል።
የህግ ጥሰቱ በአዲሶቹ የክለቡ ባለቤቶች ክሊርሌክ ግሩፕ አማካኝነት ነበር ለአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርና ለፕሪሚየር ሊጉ ሪፖርት የተደረገው።
ፕሪሚየር ሊጉ ከነሃሴ ወር ጀምሮ ምርመራ እያካሄደ ሲሆን በ2013 ክለቡን የተቀላቀሉት የዊሊያንና የሳሙኤል ኤቶ ዝውውሮች በአዲስ መካተታቸው ተዘግቧል።
የምዕራብ ለንደኑን ክለብ በ2022 የገዛው የአሜሪካው ክሊርሌክ ግሩፕ፣ ጉዳዩ አሁን ላይ በክለቡ ውስጥ ያሉ ሰዎችን እንደማይመለከት ሞግቷል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv