አዲስ አበባ | ጥቅምት 20 2016| NBC ETHIOPIA -ሳዑዲ አረቢያ የ2034 የወንዶች የአለም ዋንጫ ውድድርን እንደምታሰናዳ ተዘግቧል።

ፊፋ የ2034 የአለም ዋንጫ በኦሽንያ ወይም እስያ አህጉር ሊካሄድ እንደሚችል ማስታወቁ ይታወሳል።
ሆኖም ግን የኦሽንያ አህጉርን የወከለችው አወስትራሊያ ከጨረታው እራሷን ማግለሏን በዛሬ ዕለት ይፋ በማድረጓ ሳዑዲ አረቢያ ብቸኛዋ ተወዳዳሪ ሆናለች።
የባህረ ሰላጤዋ አገር ምንም እንኳ ከእስያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ድጋፍ ቢቸራትም፣ ከሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር በተገናኘ ከምዕራባውያን አገራትና የመንግስታቱ ድርጅት ዘንድ ተደራራቢ ክሶች እየቀረቡባት እንደመሆኑ ይህን ታላቅ ሃላፊነት መረክቧ አወዛጋቢ ሆኗል።
አገሪቱ ከ2018 ወዲህ የፎርሙላ 1፣ ጎልፍና የቦክስ ውድድሮችን ጨምሮ በርካታ የታላላቅ መድረክ ውድድሮችን አሰናድታለች።
የ2034 የወንዶች አለም ዋንጫ በክረምት ወር እንደሚካሄድ መረጃው አክሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












