አዲስ አበባ | ጥቅምት 16፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በአለም ለ44ተኛ በሀገራችን ለ36ተኛ ጊዜ ” ቱሪዝም ለአረንጓዴ ልማት ፣አረንጓዴ ልማት ለቱሪዝም በሚል መሪ ቃል የቱሪዝም ሳምንትን እያከበረ ይገኛል። ቢሮው ዘንድሮ የአለም የቱሪዝም ቀን የሚከበርበትን መሪ ቃል መሰረት በማድረግ ሲምፖዚየሙ እያካሄደ ይገኛል ።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ባለፉት አምስት አመታት እንደሀገር በቱሪዝም ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች በሴክተሩ ላይ ለውጥ ማምጣት የተቻለ መሆኑን አንስተዋል ። በቀጣይም ያሉትን የቱሪዝም መስህቦች በይበልጥ ለማስተዋወቅ ብሎም የሚፈለገውን ገቢ ከዘርፉ ለማግኘት በርካታ ስራዎች መስራት እንደሚጠበቅ ገልፀዋል ።
ሃላፊዋ አክለው የቱሪዝም ሴክተር በትስስር የሚሰራ እንደመሆኑ መጠን በቱሪዝም ዘርፍ ላይ የሚንቀሳቀሱ አካላትና የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትስስር መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል ።
በሲንፓዚየሙም ላይም በመሪ ቃሉ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው።
በሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv












