አዲስ አበባ | ጥቅምት 16፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ውፍረት ከእርግዝና በፊት በአንዲት ሴት ላይ የተለያየ የጤና እክሎችን ከማምጣቱ ባለፈ ለአንዲት ሴት እርግዝና እንዳይከሰት ከፍተኛ የሆነ ሚና ይጫወታል።

???? አንዲት ሴት ኪሎ መቀነስ ያለባት እርግዝና ከመከሰቱ በፊት ቢሆን ይመከራል። ይህም በእርግዝና ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉትን ችግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንስላታል።
???? በእርግዝና ጊዜ ውፍረት ሊያስከትላቸው የሚችላቸው ችግሮች

???? በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ግፊት( Gestational Hypertension and Preeclampsia)
???? በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኳር በሽታ(Gestational DM)
???? በእንቅልፍ ጊዜ የሚከሰት የትንፋሽ መቆራጥ(Obstructive Sleep Apnea)
???? በህፃኑ ላይ የሚከሰት የአፈጣጠር ችግር – የልብ ችግር(Heart disease) እና የአከርካሪ አጥንት ክፍተት(Neural Tube defect)
???? የህፃኑ ኪሎ መጨመር (Macrosomia) – ይህ ደሞ ወሊድ አስቸጋሪ እንዲሆን ማድረግ እና ለኦኘራሲዮን መዳረግን ያመጣል
???? ጊዜው ሳይደርስ ምጥ መምጣት
???? ፅንሱ በማህፀን ውስጥ ጊዜው ሳይደርስ መጎዳት
???? በሳምንት ምን ያህል ጊዜ መንቀሳቀስ አለብሽ?

???? በሳምንት 150 ደቂቃ መጠነኛ የሆነ ኤሮቢክስ(aerobics) መስራት ትችያለሽ። ይህ ማለት 30 ደቂቃ በቀን እንደማለት ነው።
30 ደቂቃ በአንዴ ሳይሆን ቀስ እያልሽ ከ5 ደቂቃ ተነስተሽ በየሳምንቱ 5 ደቂቃ እየጨመርን መሆን አለበት።
???? የሰውነትሽ ክብደት የሚለካው BMI (Body mass index) በሚባል አለካክ ሲሆን ይህም ክብደትሽን ከቁመትሽ ጋር በማነፃፀር ይሆናል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv












