አዲስ አበባ | ጥቅምት 06 2016| NBC ETHIOPIA – 12ኛዉ የኢትዮ ፖልተሪ ኤክስፖ፣ 8ኛዉ የአፍሪካ እንስሳት ዓዉደርዕይና ጉባዬ እንዲሁም የአፒካልቸር እና አኳካልቸር ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የንግድ ትርዒት የዘርፉን ዋነኛ አንቀሳቃሾችን በማሳተፍ በመጪዉ ጥቅምት 15-17 2016ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገለፀ።
በሁሉም የእንስሳት ሀብት የገበያ ሰንሰለቶች ላይ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወ፣ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር እንዲሁም የዕዉቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት የኔዘርላንድ ብሄራዊ ተሳትፎን ጨምሮ ከ17 ሀገራት በተዉጣጡ ጠንካራ ድርጅቶች ተሳትፎ ይካሄዳል ተብሏል።
ባለፉት ዓመታት የተካሄዱት ዓዉደርዕይ እና ጉባዬዎች ለዶሮ፣ ወተትና ስጋ ዘርፎችዕድገትና ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸዉ የተገለፀ ሲሆን አሁን ለ3 ቀናት በሚካሄደዉ ዓዉደርዕይም ከ 4000 በላይ የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጎብኝዎች ይጠበቃሉ።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












