አዲስ አበባ | መስከረም 30 2016| NBC ETHIOPIA -የሳውዲ ፕሮ ሊግ ባለስልጣናት ሊዮኔል ሜሲን በውሰት ዉል ለማዘዋወር ጥያቄ ሊያቀርቡ መዘጋጀታቸው ተሰምቷል።

ሜሲ ክለቡ ኢንተር ሚያሚ ቅዳሜ እለት በሜጀር ሊግ ሶከር ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በሲኒሲናቲ ተሸንፎ ከመድረኩ ዉጪ መሆኑ ይታወሳል።
ይህም ማለት አርጀንቲናዊው የአለም ዋንጫ አሸናፊ፣ አዲሱ የውድድር አመት እስከሚጀምር እስከ የካቲት መጨረሻ ድረስ ከውድድር ዉጪ ይሆናል ማለት ነው።
የሳውዲ ፐብሊክ ኢንቨስትመን ፈንድና የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ሰፊ የእረፍት ጊዜውን ታሳቢ በማድረግ በውሰት ዉል ለማዘዋወር የሚችሉበትን መንገድ እያጤኑ መሆናቸውን ስካይ ስፖርትስ ዘግቧል።
ሜሲ ባሳለፍነው ክረምት ወደ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ኢንተር ሚያሚ ከማቅናቱ በፊት በሳውዲ ፕሮ ሊግ ክለቦች በጥብቅ ሲፈለግ እንደነበር አይዘነጋም።
በሌላ በኩል፣ ሜሲ ለአጭር ጊዜ ወደ ቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና ሊመለስ ይችላል የሚሉ የጭምጭምታ ወሬዎች እየተናፈሱ ናቸው።
አርጀንቲናዊው የኢንተር ሚያሚ አሰልጣኝ፣ ታታ ማርቲኖ ግን የ36 አመቱ ኮኮብ ዳግም ወደ ካምፕኑ ሊመለስበት የሚችል እድል እንደሌለ አስረድተዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












