አዲስ አበባ | መስከረም 30 2016| NBC ETHIOPIA – ዋይኒ ሩኒ የበርሚንግሃም ሲቲ አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል ።

ሩኒ ለሶስት አመት ከግማሽ በሳን አንድሪው የሚያቆየውን ዉል አስሯል።
ከሩኒ በተጨማሪ የቀድሞው የቼልሲ ተጨዋች አሽሊ ኮልና የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ጆን ኦሼ አዲሱን የበርሚንግሃም ሲቲ “ኮችንግ ስታፍ” ተቀላቅለዋል።
ሩኒ ለአንድ አመት ከግማሽ ከቆየበት የሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ዲሲ ዩናይትድ ጋር የነበረው ዉል ባሳለፍነው እሁድ እለት ነበር የተቋረጠው።
የሻምፒዮን ሽፕ ተሳታፊው ክለብ በርሚንግሃም በተመሳሳይ፣ ከአንድ ቀን በፊት አሰልጣኝ ጆን ዩስታስን ከሃላፊነት ማሰናበቱ ይታወሳል።
“በርሚንግሃም ሲቲ እግር ኳስ ክለብ ዋይኒ ሩኒን በሶስት አመት ከግማሽ ዉል ለመቅጠር መስማማቱን ሲያስታውቅ በደስታ ነው”። ብሏል ክለቡ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












