አዲስ አበባ | መስከረም 30 2016| NBC ETHIOPIA – በአፍጋኒስታን ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸው ከተሰማ ከቀናት በኋላ በተመሳሳይ አካባቢ ዳግመኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የደረሰው ኼራት ተብላ ከምትጠራው ከተማ 28 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ ነው። ዛሬ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው የጉዳት መጠን እስካሁን አልታወቀም።
ቅዳሜ የተከሰተው ርዕደ መሬት በ6.3 ማግኒቲዩድ የተለካ ሲሆን፣ በጭቃ የተሰሩ ቤቶች በብዛት የሚገኙባቸው መንደሮች ላይ የከፋ ጉዳት አድርሷል።
አደጋው ከተከሰተ ቀናት ቢቆጠርም ከመንደሩ ነዋሪዎች አሁንም የደረሱበት ያልታወቁ ከ500 በላይ ሰዎችን የነፍስ አድን ሰራተኞች ከፍርስራሽ ውስጥ ለመፈለግ አካፋ እና ዶማ እንዲሁም እጃቸውን እየተጠቀሙ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መግለጹን ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












