አዲስ አበባ | መስከረም 29 2016| NBC ETHIOPIA -የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ የታክስ ስርዓትን ለማዘመን፣ የገቢ አሰባሰብን ለማሳደግና በፈቃደኝነት ግብር የመክፈል ባህልን ለማዳበር የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሲሆን ለታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅናና ምስጋና መስጠት ከእነኚህ መካከል ይገኙበታል።

በእዚህም መሰረት ለ2015 በጀት አመት ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር በማዘጋጀት ላይ ናቸው።
ለ5ተኛ ጊዜ ስለሚዘጋጀው መርሀ ግብር የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴና የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከ2011 ጀምሮ እውቅናው ሲሰጥ የቆየ ሲሆን የአሁኑ መርሃ ግብር ሚኒስቴሩ ከየካቲት 2015 እስከ የካቲት 2016 እያከናወነ ያለው የግብርና ታክስ ንቅናቄ አካል መሆኑ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ በበጀት አመቱ ከእቅዱ 98.2 በመቶ ማሳካት የቻለበት መሆኑ መርሀ ግብሩ ካለፉት ጊዜያት አንጻር ለየት ያደርገዋል ተብሏል።
ጥቅምት 1 በሚከናወነው በእዚህ መርሀ ግብር የህግ ተገዢነታቸው የተረጋገጠና፣ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የሆኑ 500 ግብር ከፋዮች ምስጋናና እውቅና እንደሚሰጣቸው ተነግሯል።
በመቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












