አዲስ አበባ | መስከረም 29 2016| NBC ETHIOPIA – የዘንድሮውንም የአለም የአዕምሮ ጤና ቀን በዛሬዉ እለት “MENTAL HEALTH IS A UNIVERSAL HUMAN RIGHT” ወይም የአዕምሮ ጤና ሁለንተናዊ የሰው ልጅ መብት ነው! በሚል መሪ ቃል የጤና ሚኒስቴር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጋራ በመሆን እያከበረ ይገኛል።

መድረኩ በዋናነት የአይምሮ ጤና ለመላዉ አካላችን ጤንነት ወሳኙን ሚና እንደሚጫወት አጢኗል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰም በበኩላቸዉ የአይምሮ ጤናን መጠበቅ ለሚኖረን ማንኛዉም አይነት እንቅስቃሴ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ብሎም እያንዳንዱ ዜጋ ፤ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስለ አይምሮ ጤና ያለን አመለካከት ሊሻሻል እና ሊያድግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በማህሌት ግርማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












