አዲስ አበባ | መስከረም 29 2016| NBC ETHIOPIA -አዲስ አበባ ከተማ የ4ኛው የሚላን ከተማ የምግብ ፖሊሲ ስምምነት (Milan Urban Food Policy Pact) ከአፍሪካ የአስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ከተማ ሆና ተመርጣለች::

የሚላን የምግብ ፖሊሲ ስምምነት ዋና አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ በየሁለት አመት የሚደረግ ነው:: ምርጫው በምገባ መርሃ ግብር የተሻለ አፈጻጸምና ተሞክሮ ያላቸው የአለም ከተሞች የሚመረጡበት ሲሆን በዚሁ መሠረት አዲስ አበባ እና የሴኔጋሏ መዲና ዳካር ከተማ ከአፍሪካ በዐቢይ ኮሚቴ አባልነት ተመርጠዋል::
ኮሚቴው የሚላን የምግብ ፖሊሲ ስምምነት ተልዕኮ እና አዋጅ በአባላቱ ፍላጎት በቀጥታ እንዲመራ እና ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ስትራቴጂያዊ ክትትል የሚሰጥ ሲሆን ከአፍሪካ የተመረጡ ከተሞች አዲስ አበባ እና ዳካር ናቸው::
የከተማ ለከተማ ትብብር እና ምርጥ ተሞክሮ ልውውጥ ለማጎልበት እና ዘላቂነት ያለው የከተማ ምግብ ስርዓት እንዲዳብር ለማድረግ በ2015 በሚላን ከተማ አስተዳደር ከ200 በላይ በሚሆኑ ከተሞች ስምምነት በተቋቋመው የሚላን የምግብ ፖሊሲ ስምምነት ከተማችን አዲስ አበባ የትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብሯ ከታላላቆቹ ከተሞች ልቆ ተሸላሚ መሆንዋ ይታወሳል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv