አዲስ አበባ | መስከረም 29 2016| NBC ETHIOPIA -ደረጃ ዶት ኮም ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር እንዲሁም ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ፣ጋር በመተባበር ሀገር አቀፍ የስራና ሰራተኛ ማገናኛ አውደ ርዕይ ሊያካሄድ ነው።

ሀገር አቀፍ አውደ ርዕዩ ከ20ሺ በላይ አዲስ ተመራቂ ተማሪዎች እና ከ3100 በላይ የሚሆኑ የሰለጠኑ የደረጃ አካዳሚ ተመራቂዎች ከ200 በላይ ከሚሆኑ ከተለያየ ዘርፍ የተውጣጡ ቀጣሪ ድርጅቶች ጋር የሚያገናኝ ይሆናል ።
የአውደ ርዕዩ አለማም ተሳታፊ ተመራቂ ተማሪዎች ከቀጣሪዎች ጋር የሚተዋወቁበት ፣መረጃ የሚለዋወጡበት ፣ብሎም የስራ እድሎችን የሚያገኙትበት መድረክ እንደሆነ አዘጋጆቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል ።
በተጨማሪም በስፋት በሀገሪቱ የሚታየው የስራ እጥረት ችግር ለመቅረፍ አዲስ ተመራቂ ተማሪዎችን ከቀጣሪ ተቋማት ጋር በማገናኘት የስራ እድሎችን የሚያገኙበትን እንዲሁም ከተለያዩ ወጣቶች ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች ጋር የሚተዋወቁበት መድረክ እንደሚፈጥር ተገልጿል ።
አውደ ርዕዩ ጥቅምት 7እና 8 በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል ።
በሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












