አዲስ አበባ | መስከረም 25 2016| NBC ETHIOPIA -ዝላታን ኢብራሆሞቪች “የማንችስተር ዩናይትድ ባለቤቶች ግሌዘሮች፣ ባሳለፍነው ክረምት የዝውውር መስኮት ለተጨዋቾች ዝውውር በቂ ገንዘብ አልመደቡም ” በሚል ከደጋፊዎች ዘንድ በሚሰነዘረው ወቀሳ እንደማይስማማ ተናግሯል።

“አሁን ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ባላውቅም ፣ ግሌዘሮች ክለቡን የመሸጥ ፍላጎት እንዳላቸው አሳይተዋል። መዋእለ ነዋያቸውን ፈሰስ እያደረጉ መሆናቸውንም ማስታወስ እፈልጋለሁ” ብሏል የቀድሞው የክለቡ አጥቂ ከፒርስ ሞርጋን ጋር በነበረው ቆይታ።
ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ በርካታ ተጨዋቾችን ማዘዋወራቸውን በማስታወስ፣ ይህም ገንዘብ እያወጡ አይደለም ለማለት አያስደፍርም ባይ ነው።
YouTube https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












