አዲስ አበባ | መስከረም 21 2016| NBC ETHIOPIA- ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚካሄደው ይህ ጉባኤ ” ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለዘላቂና ፍትሐዊ መጻኢ ጊዜ የአፍሪካ የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሐሳብ ይከናወናል።
ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ሕብረት (ITU) የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤውን ከመስከረም 22 እስከ 24/2016 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ ያካሂዳል።
ጉባኤው በአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማምጣትና የዘላቂ ልማት ግቦችን ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራል።
የአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለአህጉሪቷ መጻኢና ዘላቂ የዲጂታል እድገት እንዲሁም ለዓለም አቀፍና አህጉራዊ የልማት ግቦች መሳካት ያለው ሚና ላይ ምክክር ይደረጋል።
የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዓለም አቀፍ ተደራሽነት፣ በአፍሪካ እየተተገበሩ ያሉ የዲጂታል ትስስር ፕሮጀክቶች የአፈጻጸም ደረጃን የተመለከቱና ሌሎች ተጓዳኝ ጉዳዮች ውይይት ይደረግባቸዋል።
በጉባኤው ላይ የሕብረቱ የአፍሪካ አባል አገራት ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማትና የልማት አጋሮች ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ።
እንደ ኢፕድ ዘገባ ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ሕብረት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት አንዱ ሲሆን የተቋቋመው እ.አ.አ በ1865 ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












