
አዲስ አበባ | መስከረም 21 2016| NBC ETHIOPIA- 1. ራስ ምታት፣ አይን ብዥ ማለት ወይም መጨለም፣ ከእምብርት በላይ እና በሆድሽ በላይኛው ቀኝ ክፍል ህመም ካለ
⚠️ አስተውይ !:- በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የግፊት ምልክት ስለሆነ በቶሎ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ።
2. ከ 7 ወር በኋላ ከማህፀን የሚወጣ ደም አለ?

⚠️ አስተውይ! :- የእንግዴ ልጁ ቀድሞ ከሆነ፣ ከእንግዴ ልጁ ጀርባ ደም እየፈሰሰ ከሆነ፣ የማህፀን ኢንፌክሽ ካለ እናም ሌሎች ከባድ የሆኑ የጤና እክሎች ምክንያት ስለሚሆን በቶሎ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ::
3. በመጀመሪያዎቹ 7 ወራት ደም እና ስጋ የመሰለ ነጭ ነገር ከማህፀን መፍሰስ ፣ ከእምብርት በታች ሆድ መቁረጥ፣ የጀርባ መቁረጥ፣ ውሀ የመሰለ ፈሳሽ መፍሰስ ካለ

⚠️አስተውይ! :- የውርጃ ምልክት ሊሆን ስለሚችል የጤና ተቆምን መጎብኘት ግድ ያስፈልግሻል
4. ጆሮ መጮህ ፣ ማዞር ፣ ከፍተኛ ድካም ፣ ራስ ምታት፣ ልብ ሲመታ መታወቅ ካለ

⚠️ አስተውይ! : – እነኝህ የደም ማነስ ምልክቶች ስለሆኑ በቶሎ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይኖርብሻል፡፡
5. በመጀመሪያዎቹ 4 ወራት ከፍተኛ የሆነ ማስታወክ እና ማቅለሽለሽ ፣ ከ5% በላይ ከእርግዝና በፊት ኪሎ መቀነስ ካለሽ

⚠️ አስተውይ! :- ይህ (ማቅለሽለሽና ማስታወክ) በአብዛኞቹ እናቶች ላይ ሊታይ የሚችል ችግር ቢሆንም ነገር ግን በጣም ከፍተኛ ሲሆን እና ኪሎ መቀነስ ሲኖር የህክምና እርዳታ ስለሚያስፈልግሽ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ፡፡
6. የልጅሽ እንቅስቃሴ ከወትሮው ቀንሶብሻልን?

⚠️ አስተውይ! :- ከ5 ወር በውሀላ አብዛኞቹ እናቶች የልጃቸውን እንቅስቃሴ ማስተዋል ይጀምራሉ ይሁንና የልጅን እንቅስቃሴ የሚቀንሱ ነገሮች ብዙ ቢሆኑም የልጅሽ እንቅስቃሴ ከወትሮው በጣም ከቀነሰብሽ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች:- ውሀው መቀንስ ወይም ደሞ በጣም መጨመር ሲኖር ፣ ከማህፀን ደም ሲፈስ ፣ ፅንሱ ከእንግዴ ልጁ በታች ሲሆን ፣ ወይም የአንቺ ክብደት እና የስራ ሁኔታ እንዳይሰማሽ ካደረገ ወይም ደግሞ ልጅሽ እንቅልፍ ላይ ሲሆን ሊሆን ይችላል።ለሁሉም ግን ሀኪምሽን ማማከሩ እና ምርመራ ማድረጉ ተገቢ ነው።
7. ከ 9 ወር በፊት ድንገት በተኛሽበት ፣ ቁጭ ባልሽበት ወይም ስራ ላይ ሆነሽ ውሀ የመሰለ ወይም ሽንት የመሰለ ነገር ‘ፏ ‘ ብሎ ከመሀፀንሽ ከፈሰሰ

⚠️አስተውይ!:- ይህ የእንሽርት ውሀ ሰለሆነ ቶሎ ብለሽ ወደጤና ተቋም ሂጂ አለበለዚያ ለተለያዩ አደጋዎች ልትጋለጭ ትችያለሽ ለምሳሌ የህፃኑ እትብት ሊወጣና እና መታፈን ፣ ለመሀፀን ኢንፌክሽን መጋለጥ እና ለደም መፍሰስ ልትጋለጪ ትችያለሽ::
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት